የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና
ፓርቲያችንን በተመለከተ ማንኛውንም መረጃ በፍጥነትና በጥራት የሚያገኙበት !!
Party message Addis AbabaAbaba
ወረዳ 02 ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳኛችው ሹመት
ኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 02 በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ካሉት ከ121ዱ ወረዳዎች ውስጥ አንዱ ነው። እስከ እ.ኤ.አ 2011 ባለው መረጃ መሠረት የሕዝብ ብዛቱ ከ 55000 በላይ ነው።
"የላፍቶ ማስታወሻ"
"የላፍቶ ማስታወሻ" :- በስራ ዕድል ፈጠራ እና በሌማት ቱሩፋት ስራዎች የነበሩ ጉድለቶችን የሚያካክስ ርብርብ ይጠበቅብናል - አቶ ሞገስ ባልቻ
በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የስራ ዕድል ፈጠራ እና የሌማት ቱሩፋት የሶስት ወራት የንቅናቄ ዕቅድን የ60 ቀናት አፈፃፀም ገምግመዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት የስራ ዕድል ፈጠራ እና የሌማት ቱሩፋት የኑሮ ውድነትን የሚያቃልሉ ፣ ሰው ተኮር ስራዎችም የሚጠናከርበት በመሆናቸው የሁሉም አመራር የርብርብ ማዕከል ናቸው ብለዋል::
የሌማት ቱሩፋት እና ለስራ ዕድል ፈጠራ ፀጋዎችን አሟጦ መጠቀም የፓርቲያችን ኢኒሼቲቪ መሆናቸውን ያስረዱት አቶ ሞገስ ግለቱን ጠብቆ እንዲጓዝ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አስረድተዋል።
የፓርቲ አመራሮችም ስራዎችን አቀናጅተው ሊመሩት እንደሚገባ ያሳሰቡት ኃላፊው በተለይም በስራ ዕድል ተጠቃሚነት ላይ ያልተቀረፈውን የአመለካከት ማነቆው ለመፍታትም ባለድርሻ አካላት ርብርባቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የሌማት ቱሩፋት ፀጋዎቻችንን ገና እንዳልተነኩ የስረዱት አቶ ሞገስ ላፍቶ ክ/ከተማ ላይ በዛሬው ዕለት በጥልቀት የተገመገሙ የስራ ዕድል ፈጠራ እና የሌማት ቱሩፋት ስራዎችን ጉድለቶችን የሚያካክሱ ተግባራትን በማከናወን የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ መረባረብ እንደሚገባም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ የፓርቲ እና የሴክተር ተቋማት አመራሮች ቅንጅታዊ ጥረት የንቅናቄ ዕቅዱ ይፋ በተደረገባቸው ባለፉት ሁለት ወራት በርካታ ውጤቶችን ማስገኘቱን ጠቅሰዋል።
አዲስ አበባ አምራችም ጭምር እንጅ ሸማች ብቻ አይደለችም በሚል በሌማት ቱሩፋት ፣ በከተማ ግብርና የተጀመረው እንቅስቃሴ ሊቀዛቀዝ እንደማይገባው ያስረዱት አቶ ጥራቱ በየክ/ከተማው ፀጋዎችን በአግባቡ መጠቀም ላይ ያሉ ሰፋፊ ችግሮች ሊቀረፉ ይገባል ብለዋል።
ለክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራ ቅንጅታዊ ርብርብ ይጠይቃል ያሉት ኃላፊው የስራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር ለሌሎችም የስራ ዕድል መፍጠር የሚያስችላቸውን አቅም እንዲያገኙ ኢንተርፕራይዞችን ማደራጀት ላይም ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል።
በስራ ዕድል ፈጠራ እና በሌማት ቱሩፋት ባለፉት ሁለት ወራት ወደ ኋላ የቀሩ ተቋማት የተመሩበትን አግባብ እና የገጠሟቸውን ተግዳሮቶች የውይይቱ ተሳታፊዎች የጠቀሱ ሲሆን ጉድለቶችን ፈጥነው በማረም ዕቅዶቻቸውን ለማሳካት ቅንጅታቸውን በማጠናከር እንደሚረባረቡ አረጋግጠዋል።
በከተማችን እየተፈጠሩ ያሉትን የስራ ዕድሎች ተጠቅሞ የራስን እና የቤተሰብን ህይወት ማሻሻል እየተቻለ ስራን በማማረጥ የተዘባ አመለካከት ጊዜያቸውን የሚያባክኑ ግለሰቦችም ስላሉ ከቤተሰብ ጀምሮ ቅንጅታዊ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባም ተመላክቷል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ /ቤት
የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛው መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ኮንፈረንስ ከተማ አቀፍ ማጠቃለያ
የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛው መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ኮንፈረንስ በከተማ ደረጃ የአዲስ አበባ ከንቲባ ክብርት አዳነች አቤቤ፣ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ ሌሎችም የስራ ኃላፊዎች የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ሀደ ስንቄዎች፣ የፓርቲያችን አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
በየደረጃው ውስጠ ዴሞክራሲን በሚያጎለብት መልኩ በድምቀት ሲካሄድ የቆየው የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛው መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ኮንፈረንስ ከተማ አቀፍ ማጠቃለያ በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር፣ በህብር ውበት፣ በህፃናትና ታዳጊዎች ህብር ዝማሬዎች፣ በታዳጊዎች ሰርከስ እና በሌሎችም ህብረ ብሔራዊነትን በሚያንፀባርቁ ፕሮግራሞች በድምቀት መካሄድ ጀምሯል ።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ ፅ / ቤት
" የፓርቲ አቅሞቻችንን ለተሳለጠ የመንግስት አገልግሎት ! "
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የ 2017 ዓ/ም በጀት ዓመት የስድስት ወራት የፖለቲካ እና የድርጅት ስራዎች አፈፃፀምን መገምገም ጀምረዋል።
በግምገማው ጠንካራ ፓርቲ በመገንባት ለጠንካራ መንግስት አቅም ለመሆን የተቀመጠውን አቅጣጫ ተከትሎ በመደበኛ እና በንቅናቄ ስራዎች ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ስራዎች አፈፃፀም የጋራ ይደረጋል ፤ ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይም የጋራ ግንዛቤ ይያዛል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በግምገማዊ ውይይቱ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት ግምገማው የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ከተማ አቀፍ ኮንፈረንሶች በተካሄዱበት ማግስት የሚካሄድ መሆኑን ጠቁመዋል።
በእሳቤ ፣ በአደረጃጀት ፣ በገቢራዊነት የገዘፈው ብልፅግና ፓርቲ በመጀመሪያው ታሪካዊ ጉባኤው ያስቀመጠውን ጠንካራ ፓርቲ ለጠንካራ መንግስት አቅጣጫ ለማሳካት ርብርብ ሲደረግ መቆየቱንም አውስተዋል።
የብልፅግና ፓርቲን የሀሳብ ፣ የአደረጃጀት ፣ የህብረ ብሔራዊ አብሮነት እንዲሁም የልማት ስታንዳርድ ከፍ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ የገለፁት አቶ ሞገስ በልማቱ ባሰካነው ውጤት ልክ በአገልግሎት አሰጣጡም እመርታን ለማስመዝገብ ውስጣችንን በመፈተሽ ተቋሞቻችን አብነት ለማድረግ ቁርጠኝነትን መላበስ ይገባል ብለዋል።
የፓርቲ አቅምቻችንን ለተሳለጠ የመንግስት አገልግሎት መሳለጥ በማዋል በቀጣይ በልዩ ትኩረት በመስራት የአዲስ አበባን ሁለንተናዊ የብልፅግና ተምሳሌትነት ለማረጋገጥ በዛሬው ግምገማም የጋራ ግንዛቤ እንደሚያዝ አስገንዝበዋል።
በግምገማዊ ውይይቱ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊ እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ ፣በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ እንዲሁም የክ / ከተማ እና የወረዳ የፓርቲ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት
'' ከቃል እስከ ባህል ! "
ዛሬ የብልፅግና ፓርቲ ቅድመ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ከተማ አቀፍ የማጠቃለያ ኮንፈረንስ አካሂደናል።
ብልፅግና አሻግሮ የሚመለከት ፣ የሚፈፅመውን የሚናገር ፣ የተናገረውን የሚፈፅም ተግባሩ እና ቃሉ ተመሳሳይ መልክ ያለው ግዙፉ ፓርቲ ነው !
በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ እንደ ወርቅ ተፈትኖ ነጥሮ እየወጣ ፣ ፈተናዎችን ወደ ድል እየለወጠ ፣ የኢትዮጵያን ታሪካዊ ስብራቶች እየጠገነ ፣ ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ራዕይውን ለማሳካት እየተጋ የሚገኘው ፓርቲያችን የሚታዩ ፣ የሚዳሰሱ ተጨባጭ ውጤቶችን አስመዝግቧል።
በመጀመሪያው ታሪካዊ ጉባኤው ጠንካራ ፓርቲ በመገንባት ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለማፅናት እና የህዝባችንን ውስብስብ ችግሮች በመፍታት የኑሮ ደረጃቸውን ለማሻሻል ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ቀን እና ሌት ፣ 7 / 24 የሥራ መርህ የከተማችንን የልማት ጥማት የሚያካክስ ርብርብ ስናደርግ ቆይተናል ፤ በላብአችን ጠብታ ውጤቶችንም አስመዝግበናል።
የፖለቲካ ባህላችንን ወደ ውይይትና ትብብር ለማምጣት እንደ ፓርቲ ታሪካዊ እርምጃዎች ተወስደዋል።
ወንድማማችነት ፣ እህትማማችነት እና ህብረ ብሔራዊ አብሮነት እንዲጎለብት የተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ፍሬ ማፍራት ጀምረዋል።
አካታቹን የብሔራዊነት ትርክት በመገንባት ሀገረ መንግስት ግንባታውን ለማፅናት ለተጀመረው ርብርብም ፓርቲያችን እና መንግስታችን የሚጠበቅባቸውን እየተወጡ ይገኛሉ።
ፓርቲያችን ብልጽግና ባለፉት ዓመታት ለውጡን የሚገዳደሩ በርካታ ፈተናዎች ቢገጥሙንም እንኳን በኢኮኖሚው፣ በማህበራዊ እንዲሁም በውጭ ጉዳይ ፓሊሲዎቻችን አስደማሚ ውጤቶችን ማስመዝገብ ችለናል።
ብልፅግና ቃሉን እየተገበረ በየዘርፉ ስኬታማ ተግባራትን ባህል እያደረገ የሚጓዝ ሲሆን ከጉባኤ እስከ ጉባኤ የሚተገበሩ የሁለተኛው መደበኛ ጉባኤ አቅጣጫዎችንም በ7 / 24 ትጋታ በመፈፀም የላቀ ድል ለማስመዝገብ ቃላችንን እናድስ።
እንኳን አደረሳችሁ ! እንኳን አደረሰን !
" ከቃል እስከ ባህል ! "
"ከቃል እስከ ባህል!!"
ከጉባኤ እስከ ጉባኤ ያሳካናቸውን ስኬቶች እያስቀጠልን የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና እናረጋግጣለን !!
ብልፅግና ሀገራችን የነበረባትን ስብራቶች በውል በመገንዘብ እና ስብራቶቹን ጨርሶ ሊያድን የሚችል ርዕዮትና ፍኖተ ካርታ በመንድፍ ብሎም አባሉንና ህዝቡን ከጉን በማሰለፍ ይሁኝታን ያገኙ በርካታ ስኬቶች በሁሉም መስክ ማምጣት ችሏል።
እነዚህ ተጨባጭ ስኬቶች ደግሞ በምቹ መደላደል ውስጥ የሙጡ ሳይሆን ፓርቲው ለቆመለት አላማና ለገባው ቃል የታመነና ቁርጠኛ በመሆኑ ያጋጠሙትን ፈተናዎች በጥበብና በስክነት እያለፈ በብዙ ትጋትና ጥረት ያመጣቸው ናቸው።
አሁን የደረስንበት ስኬቶች ምናልባት የውስጥና የውጭ እንዲሁም ተፈጥሮ ተደራርበው ባይፈትኑት ኖሮ አሁን ከተገኙ ውጤቶች አንጻር ልንደርስበት የምንችለው ስኬት ምን ሊሆን እንደሚችል ማሰብ አይከብድም።
ፓርቲያችን ከለውጡ ጀምሮ በመጀመሪያ ጉባኤ ያስቀመጣቸውን አንኳር ነጥቦች እየመነዘረ መስራት ችሏል። በቀጣይም ያሉትን ስኬቶች እንደ ልምድ ወስደን የጎደሉ ስራዎች ላይ በ2ኛ መደበኛ ጉባኤ መፍትሔ አብጅተን የጀመርነውን የብልፅግና የስኬት ጉዞ በፍጥነትና በፈጠራ አጅበን በህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት አሰናስነን በተባበረ ክንድ ብልፅግናችንን ለማረጋገጥ እንተጋለን።
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ባህል ኪነጥበብ ቱሪዝም ፅህፈት ቤት "አዲስ ምህዋር" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የስዕል አውደ -ርዕይ ተከፈተ።
የክፍለ ከተማው ባህል ኪነ ጥበብ ቱሪዝም ፅህፈት ቤት የተዘጋጀው "አዲስ ምህዋር" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የስዕል አውደ -ርዕይ በክፍለ ከተማው ቅጥር ግቢ በዛሬው እለት ተከፍቶ ለእይታ በቅቷል።
ኤግዚብሽኑን የክፍለ ከተማው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሙሉጌታ ጉሉማ፣ ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሒም መሀመድ ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ተከፍቷል።
በአውደ ርዕዪም ሀገራዊ ገፅታ የሚያመለክቱ ፣ሀይማኖታዊ ክንውኖች፣ ሀገራዊ ቅርሶች፣ ባህላዊ ጨዋታዎች የሚያሳዩ ስዕሎች በሰአሊ ሲሳይ ወርቁ፣ በሰአሊ ፌቬን ከድር፣ በልዩ ፍላጎት ሰአሊያን አማካኝነት ለእይታ ቀርበዋል።
የክፍለ ከተማው የባህል ኪነጥበብ ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሙልጌታ ብርሀኑ እንደገለፁት በክፍለ ከተማ ደረጃ በተዘጋጀው አውደ ርዕዩ ተሳታፊ የሆኑ ከየካቲት 03 እስከ የካቲት 09 በከተማ ደረጃ በሚካሔደው የኪነጥበብ ፌስቲቫል ክፍለ ከተማውን ወክለው ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።
የስዕል አውደ ርዕዩም ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 2 ቀናት እንደሚቆይ ተናግረዋል።
በኮ/ቀ/ክ/ከተማ የወረዳ 02 የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአባላት መረጃ
ወረዳ አመራር...33 + ወጣት ክንፍ... 560+ ሴት ክንፍ...1386+
ጥቃቅን... 236 + ቢሮ .... 142 + አርሶ አደር ....44 +
ነጋዴ...31 + ባለሀብት...18 + ት/ቤት... 204 +
መኖሪያ.... 567 + ወረዳ አመራር...33 + ድምር ...3128 +