ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ ወረዳ 02 ብልጽግና ፓርቲ
የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና
መደበኛ እና የንቅናቄ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎችን በአግባቡ በመፈፀም ወደ ላቀ ውጤት ማሸጋገር ያስፈልጋል !!
ኮልፌ ወረዳ 02 ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ
መጋቢት 15/2017 ዓ.ም
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር የንቅናቄና መደበኛ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች አፈፃፀም ያሉበትን ደረጃ በአጠቃላይ አመራር ግምገማ ተደረገ።
በመድረኩም ከመንግስት ስራዎች አንፃር የስራ እድል ፈጠራ ፣ የሌማት ትሩፋት ፣ የቀዳማይ ልጅነት እንዲሁም በየብሎኩ የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመፍታት አንፃር ያሉ ጉዳዮች የታዩ ሲሆን ከፓርቲ ስራ አንፃር የአባላት ምልመላ የብልፅግና ቤተሰብ ውይይቶችና የፓርቲ አቅጣጫዎች አተገባበር ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል።
በግምገማውም የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሰፋ ነጋሳ እንደገለፁት በመደበኛና በንቅናቄ ከተያዙ እቅዶች የስራ ዕድል ፈጠራና የከተማ ግብርና ስራዎች በተሻለ ደረጃ እየተሰሩ ቢገኙም ከእቅድ አንፃር እንዲሳካና ከዚያ በላይ መፈፀም እንዲቻል ሁሉም አመራር ርብርብ ማድረግ ይገባዋል በማለት ሌሎች ተግባራትንም በጊዜ የለኝም መንፈስ መፈፀም እንደሚገባ አሳስበዋል።ከዚህም በተጨማሪ ከጥቂት ቀናት በኋላ የሚከበረው የረመዳን በዓል አቅም ለሌላቸው ነዋሪዎች ማዕድ ለማጋራት እየተሰራ ያለው ስራ ላይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በመቀጠልም የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ሹመት እንደገለፁት በወረዳው በንቅናቄ እየተሰሩ ካሉት የስራ እድል ፈጠራ እና የክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ኢንሼቲቭ የሆኑት የከተማ ግብርና ተግባራት ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተሰሩ እንደሆነ ጠቁመው በቀሪ ጊዜያት በተሻለ መነሳሳት የወረዳው ነዋሪዎች እንዲጠቀመሙ አመራሮች ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል። አያይዘውም የፓርቲ ስራዎችን ሁሉም አመራር በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በመፈፀም ውጤት ማምጣት እንደሚገባው ገልፀዋል።
በመጨረሻም በእቅድ የተያዙ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎችን በተሻለ ሁኔታ መፈፀም እንዲሁም ያሉ ምቹ ሁኔታዎችን እንደ ፀጋ በመውሰድ ተግባራትን በውጤት ማሳካት ይገባል ሲሉ የወረዳው ዋና ስራ አስፃሚ አቶ አሰፋ ነጋሳ አበክረው አስገንዝበዋል፡፡
ታላቁ የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ በክፍለ ከተማው አስተዳደር የኢፍጣር መርሀ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ኮልፌ ወረዳ 02 ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ
መጋቢት 14 / 2017 ዓ.ም
አስተዳደሩ በዛሬው እለት በክፍለ ከተማችን ከሚገኙ አቅመ ደካሞች እና ዝቅተኛ ገቢ ካላቸዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር የኢፍጣር መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል።
"የታላቁ የረመዳን ፆም የአብሮነትን፣ ወንድማማችነት እና እህትማማችነትን እንዲሁም የእርስ በእርስ የመደጋገፍ ባህል ማሳያ ነው" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የኢፍጣር ፕሮግራም የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወይዘሮ ቡዜና አልከድር እና የክፍለ ከተማው እስልምና ጉዳዮች ምክትል ስራ አስፈፃሚ ኡስታዝ አህመድ ዓሊ ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የተለያየ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የከተማ እና የክፍለ ከተማ አመራሮች፤ የመጅሊስ አመራሮች እና የእምነቱ ተከታዮች ተገኝቷል ፡፡
የብሔራዊነት ገዢ ትርክትን በማስረፅ ለአስተማማኝ ሀገረ-መንግስት ግንባታው ሚናችንን እንወጣለን !
ኮልፌ ወረዳ 02 ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ
መጋቢት 10 / 2017 ዓ.ም
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ለወረዳው የብልፅግና ህብረት ፣ ቤተሰብና አባላት "የብሔራዊነት ገዢ ትርክትን በማስረፅ አስተማማኝ ሀገረ-መንግስት የመገንባት ሂደትን ስኬታማ ለማድረግ የአባላት ሚና ወሳኝ ነው " በሚል ርዕስ ስልጠና ሰጠ።
የብልፅግና ህብረትና ቤተሰብ እንዲሁም የአባላትን አቅም የሚያጠናክሩ የጋራ እሳቤዎች ላይ የተደራጀ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ ትልቅ ሚና እንዳለው ያስገነዘቡትና ስልጠናውን የሰጡት የክፍለ ከተማው ምክትል ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አደም መሀመድ በስልጠናው ሉዓላዊ ክብሯን ጠብቃ ያለች ኢትዮጵያን ለመገንባት የገዢ ትርክትን ማስረፅ አስፈላጊ ነው ስለሆነም ዛሬ የተሰጡ አይነት ስልጠናዎችን በሁሉም አካባቢ በማጠናከር በተግባር የምንስማማባት ሰላማዊና በዜጎቿ የተከበረች ሀገር እንድትገነባ የድርሻችንን መወጣት ይኖርብናል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላፈዋል ።
በመቀጠልም የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ሹመት በመልዕክታቸው ገዢ ትርክት አንድነቷ የተጠበቀች ሀገር ለመገንባት እና የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለማነፅ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው ያሉ ሲሆን አክለውም ጠንካራ ሀገር ለመገንባት አማካይ የሆነ እሳቤ በማራመድ ብሔራዊ ገዢ ትርክትን ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመው ሁሉም አባል የገዢ ትርክትን በአስተማሪ ትላንት ላይ በመገንባትና ዐርበኝነትን ለብሔራዊነት በመጠቀም የበኩሉን ሚና መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በስልጠና መድረኩ የወረዳው አስተባባሪዎች፣አጠቃላይ አመራሩና የብልፅግና ህብረትና ቤተሰብ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን ጥያቄዎችና ሰፋ ያለ ውይይትም በስልጠናው ተደርጎ ከመድረክ ማጠቃለያ በመስጠት ተጠናቋል።
አመራሩ ተግባራትን በቁርጠኝነት በመምራትና ተልዕኮዎችን በውጤት በመከወን ወደ መዳረሻችን በፍጠነት መጓዝ እንድንችል ስራዎችን በወቅቱ መገምገም አስፈላጊ ነው።
ኮልፌ ወረዳ 02 ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ
መጋቢት 13/ 2017 ዓ.ም
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች በክላስተር ግምገማ የተደረገ ሲሆን በመደበኛና በንቅናቄ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በግምገማው ተዳሰዋል።
የወረዳው የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ እና የክላስተሩ አስተባባሪ ወ/ት ዘቢባ ዑስማን ጥቅል በክላስተሩ ቀጠናዎች እየተሰሩ ያሉት የስራ እድል ፈጠራ ፣ የሌማት ትሩፋት ፣ የኢሲዲ ፣ የመልካም አስተዳደር እና የፓርቲ መደበኛ ስራዎች የቀጠናዎችን ሪፖርት መነሻ በማድረግ በጥንካሬና በውስንነት ያሉ ጉዳዮችን አመላክተው የተጀመሩ የመንግስት እና የፓርቲ ተግባራት አጠናክሮ በማስቀጠል ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል በግምገማውም ሰፋ ያለ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከመድረክ ቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጦ ስብሰባው ተጠናቋል ።
በምቹና ሳቢ ግቢ የተቀላጠፈና የተሻለ የአንድ ማዕከልን ጨምሮ በሁሉም ተቋሞቻችን ለህብረተሰባችን አገልግሎት እንሰጣለን !
ኮልፌ ወረዳ 02 ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ
መጋቢት 12/2017ዓ.ም
የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሰፋ ነጋሳ በተገኙበት እየተሰጠ ያለው የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የነዋሪዎችን ጊዜ ጉልበትና አላስፈላጊ መጉላላት በማስቀረት ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተወጣ መሆኑን ተገልጋዩ ህብረተሰብ ምስክርነቱን እየሰጠ ይገኛል።
በተመሳሳይ ሌሎች የሴክተር ተቋማት አመራሮችም በቢሯቸው ተገኝተው ተገልጋዮችን በማስተናገድ ላይ ይገኛሉ። የባለጉዳይ ቀን የማህበረሰቡን ጥያቄ ከመመለስ አኳያ የላቀ ሚና እየተወጣ ይገኛል።
በአዲስ ገፅታ ወደ ሁለንተናዊ ከፍታ፦ አዲሷ አዲስ አበባ!
ብልጽግና ልዕልና መር በሆነ ትውልድና ዘመን ተሻጋሪ ዕሳቤ በወል ዕውነት የወል ሀገር ግንባታ ላይ ይገኛል። የነበሩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ስብራቶችን በማረም የትናንትን እርሾ ወረት አድርጎ በዛሬ ህብረብሔራዊ የተደመረ ትጋት ነገን እየገነባ ለትውልድ ምንዳን ያሻግራል። በሰው ተኮር የመደመር መርህ ህብረብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ላይ በመጽናት ብሔራዊነትን መሰረት አድርጎ ከሁሉም በሁሉምና ለሁሉም የሆነች ልዕናዋ የተበሰረ ሀገርን ዕውንነት ያረጋግጣል።
አዲስ አበባን የኢትዮጵያና የአፍሪካ ብልጽግና ተምሳሌት ከማድረግ አኳያ እጅግ አመርቂ የሆኑ ዕመርታዎች ተመዝግበዋል። አዲሷ አዲስ አበባ ስምና ክብሯን በሚመጠን ደረጃ ዘመንን የዋጀ አስደማሚ ገፅታን መላበስ ችላለች። የጠራ ህልምና መዳረሻ ግብ ያለው ፓርቲያችን በልህቀት በማሰብ በጥራትና ፍጥነት በመትጋት ዕጅን በአፍ የሚያስጭን ዘርፈብዙ ድሎችን አሳክቷል። መዲናዋ አዲስ አበባ ከፍ ብላ በመብረር ብልጽግናዊ ተምሳሌትነቷን እያበሰረች ለአፍሪካዊያንም ኩራት ለነዋሪዎቿም ክብር እና ምቹ መሆን ጀምራለች።
ፓርቲያችን ሰው ተኮር ነውና በርካታ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለብዙ ወጣቶች፣ ሴቶችና አቅመደካሞች የስራ ዕድል መፍጠር፣ መመገቢያ ማዕከላትና መጠላያ ሆነዋል፤ ታሪክን አክብሮ አዲስ ታሪክን መስራት መለያው ነውና ደማቅ ታሪካዊ አሻራን በማኖር አድዋን የሚዘክር ታሪካዊ ሙዜየምን ገንብቷል፤ ፓርቲው በትናንት የተቸከላ ባለመሆኑ ነገን ታሳቢ ያደረጉ የሳይንስና ቴክኖሎጅ ማዕከላትና ትውልድ የሚታነፅባቸው ቤተመጽሃፍት ት/ቤቶችን በመገንባት አዲስአበባን የተሞክሮ ማዕከል አድርጓታል።
ከተማዋ በአስተደማሚ ፍጥነትና ጥራት በመታደስ ወደ የሚመጥናት ከፍታ በአድስ ገጽታ እየተዋበች ነው። የአፍሪካ መዲናና የዓለምዓቀፍ ዲፕሎማት መቀመጫ እንደመሆኗ ወደ ትልቁ ከፍታዋ በአስደማሚ ፍጥነት እየገሰገሰች ተምሳሌታዊ ብልጽግናዋን እያፀናች ትገኛለች። በተለይም ዘመንን በዋጀ የዘመኑ ትውልድ የአርበኝነት ትጋት ማሳያ የሆነው የኮሪደር ልማት ተዓምራዊ የሚባል ገፅታን አጎናፅፏታል።
በመደመር ትጋት በህብረብሔራዊ አርበኝነት ብልጽግናዊ ህልም እያበበች የምትገኝ አፍሪካዊት ኮከብ የሆነች ውብ ከተማ፦ አድስአበባ! አሁን የጥንቷ ከተማ ስምና ክብሯን በሚገልፅ አግባብ ከፍ ብላ ደምቃለች፤ በአዲስ ገፅታ በአስተደማሚ ፍጥነት እጅን በአፍ የሚያስጭንደረጃ ላይ ትገኛለች። መደመር ከዚህ በላይም አርቆ በማሰብ አልቆ ይፈጽማልና ከከፍታችን ጥግ ለመድረስ ዘመንን በሚመጥን አርበኝነት እየተጋን ወደ ላቀ ከፍታ እንሻገራለን።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ''ከተረጅነት ወደ ምርታማነት'' በሚል መሪ ቃል የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች ለማስመረቅ ሙሉ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ ።
የክፍለ ከተማው ስራና ክህሎት ፅ/ቤት በከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት ተጠቃሚ የሆኑ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ከ11ዱም ወረዳዎች የተውጣጡ ከ2330 በላይ አባዎራዎች እና እማዎራዎች ወይም 8552 የሚሆኑ ተጠቃሚዎች በነገው እለት በከተማ ደረጃ ለማስመረቅ ሙሉ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቀዋል።
የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም መሀመድ እንዳስታወቁት የሴፍትኔት ፕሮግራም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውና በርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ያለባቸውን ዜጎች የመደገፍ አላማ እንዳለው በማስታወስ ከዚህ አንፃር በክፍለ ከተማው ከ2330 በላይ አባወራዎች እማወራዎች ወይም ከ8552 በላይ ተጠቃሚዎች በማስመረቅ የስራ እድል ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።
የሴፍትኔት ፕሮግራሙ በአካባቢ ልማት ስራዎች፣ የቀጥታና የኑሮ ድጋፍ ላይ ትኩረት ያደረገ እንደሆነ ማወቅ ተችሏል።
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሁሉም ቀጠና ካሉ የመኖሪያ መሰረታዊ ድርጅት አመራሮች ጋር የ2017 ዓ.ም በ6 ወሩ የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት ተገመገመ።
የግምገማ መድረኩን የመሩት የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ረታ ጌትዬ እንደገለፁት በ2017 ዓ.ም በመጀመሪያው 6 ወር የተሰሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ እንደሆኑ ጠቁመው በተለይም የአባላት ግንባታ ፣ መልሶ ማደራጀት ፣ የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት ስልጠና ፣ የህዋሳት ውይይቶች ላይ የተሻለ ውጤቶች እንደመጡ አመላክተዋል። አያይዘውም በውስንነት የታዩ ጉዳዮች በቀጣይ መሻሻል እንዳለባቸው ገልፀዋል።
በውይይቱም የመሰረታዊ ፓርቲ አመራሮች እንዳነሱት አሁን ላይ ስራዎች በጋራ መድረክ እየተገመገሙ መሄዳቸው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ያሉ ሲሆን ኮር አመራሩም የጀመራቸው ድጋፎች የሚበረታታና በሌሎችም ማህበራዊ መሰረት ተሞክሮው መስፋት እንዳለበት ጠቁመዋል። በመጨረሻም የመደመር ትውልድ መፅሐፍት ስጦታ ለሁሉም አመራሮች የማበርከት መርኃ-ግብር ተከናውኖ የግምግማ መድረኩ ተጠናቋል።
ኮልፌ ወረዳ 02 ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ
ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም
ሰላም የህልውናችን መሰረት የብልጽግናችን ምሰሶ ነው!
==============+++++++=============
የሰላም አስፈላጊነት ለዜጎች ሰላማዊ እንቅስቃሴና አጠቃላይ ሀገራዊ ዕድገት እጅግ የላቀ ነው። በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር "ዛሬም ለሰላማችን ዘብ ነን" በሚል መሪ ቃል የሰላም ሰራዊት አባላት ከፀጥታ አካላት ጋር በተቀናጀ ሁኔታ የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ። በቀጣይ ቀናትና ሳምንታት የሚከበሩት የገና ፣ የከተራና የጥምቀት በዓላት ፍፁም ሰላማዊ ሆነው ባህላዊና ሀይማኖታዊ ዕሴታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ የሰላም ሰራዊት አባላት ከፀጥታ አካላት ጋር በማቀናጀት የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ ላይ እንደሚገኙ የገለፁት የወረዳው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሽመልስ ሙለታ በቀጣይም በተጠናከረ መንገድ ጥበቃው እንደሚቀጥልም አሳውቀዋል።
ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ አጠንክረን ልንጠብቀው የሚገባ ሲሆን የሀገር ዕሴት የሆኑት ባህላዊና ሀይማኖታዊ በዓላትም በሰላም እንዲከበሩ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና መወጣት ይኖርበታል!
በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የድጋፍ ውል ፊርማና ሰነድ ርክክብ መርኃ ግብር ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ከትላንት የቀጠለው መርኃ ግብር ዛሬ ደግሞ የሴት ሊግ መሰረታዊ ድርጅትን የተሻለ የመረጃ አያያዝና ቅብብሎሽ እንዲኖር መረጃን በመሰነድ በአግባቡ ርክክብ በማድረግና ሞዴል መሰረታዊ ድርጅት ለመፍጠር በሚል የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ የሴት ሊግ መሰረታዊ ድርጅት ደጋፊ አመራሮች ጋር ውይይት ተደርጓል። የውይይትና የርክክብ መርኃ-ግብሩን የመሩት የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ሹመት እና የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ት ዘቢባ ዑስማን ሲሆኑ በጥቅል አለማው ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎ ሁሉም ቀጠና ላይ ደጋፊ አመራሮች በተገኙበት የሰነድ ርክክብ ፊርማ መርኃ ግብር ተከናውኗል። የርክብብ መርኃ ግብሩም በሁሉም ማህበራዊ መሰረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል ።
ኮልፌ ወረዳ 02 ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ
ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም
"የህዝባችንን ማህበራዊ ችግር ለመቅረፍ አምራች ኢንዱስትሪያሊስቶቻችንን የማሳተፍ ስራ አጠናክረን እንቀጥላለን "
ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ
በዛሬው እለት በክፍለ ከተማው ወረዳ 09 አስተዳደር የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት አቶ ጃንጥራር አባይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ አቶ ሙሉጌታ ጉሉማ የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና ሌሎች የክፍለ ከተማና ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት አስጀምረዋል።
ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ በቴዎድሮስ ፍቅሩ ኢንዱስትሪ በጎፍቃደኝነት የሚገነባው ቤት እድሳት ማስጀመሪያ ላይ የህዝባችንን ማህበራዊ ችግር ለመቅረፍ አምራች ኢንዱስትሪያሊስቶቻችንን የማሳተፍ ስራ አጠናክረን እንቀጥላለን ያሉ ሲሆን ቤቶቹ በአጭር ጊዜ ተገንብተው እንዲያልቁ አቅጣጫ በማስቀመጥ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።
የክፍለ ከተማው የኢንዱስትሪ ልማት ፅህፈት ቤት በዛሬው እለት የአምራች ኢንዱስትሪዎች ኤግዚቢሽን ያስጀምራል።
Heads of Government Ethiopia
Abiy Ahmed Ali : Abiyi Ahmed Alii; Amharic: ዐቢይ አሕመድ ዐሊ; born 15 August 1976) is an Ethiopian politician serving as the third Prime Minister of Ethiopia since 2018, and as the leader of the Prosperity Party since 2019.[1][2] He was awarded the 2019 Nobel Peace Prize “for his efforts to achieve peace and international cooperation, and in particular for his decisive initiative to resolve the border conflict with neighbouring Eritrea“..
The president of Ethiopia is the head of state of Ethiopia. The position is largely ceremonial with executive power vested in the Council of Ministers chaired by the prime minister. The current president Taye Atske Selassie Amde (Amharic: ታዬ አጽቀሥላሴ, born 13 January 1956) is an Ethiopian diplomat and politician who is serving as president of Ethiopia since 7 October 2024. He has worked as ambassador on numerous occasions in the United Nations. Prior to assuming this role, he served as the Minister of Foreign Affairs.
Adanech Abebe : Adaanach Abeebee) is an Ethiopian politician and attorney who is serving as the thirty-second mayor of Addis Ababa since 2021. She has been serving as a deputy mayor from 2020 until 2021. She previously was the Minister of Revenue and Customs Authority from 2018[1][2] to 2020, when she became the first female to assume the role of the Federal Attorney General of Ethiopia.[3][4][5][6] She is the first woman to hold the mayorship since it was created in 1910.[
ራእይ
ተልእኮ
እሴት